እንኳን ወደ ድህረ-ገፃችን በሰላም መጡ

image
+251-118691002
+251-911214983

የአዲስ አበባ የጤና ስፖርት ማህበር

የጤና ስፖርት የግለሰቦችን ጤና ከመጠበቅም በላይ ለሀገር እድገት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ያደጉት ሀገራት በጤና ስፖርት ዘርፍ ሀገርን የሚወክሉ የጤና ስፖርት ብሔራዊ ቡድኖችን ከ35 ዓመት በላይ በሆኑ ግለሰቦች መስርተዋል፡፡የአዲስ አበባ የጤና ስፖርት ማህበር በኢትዮጵያ የተቋቋመ የመጀመሪያው የጤና ማህበር ሲሆን ከተመሰረተ እነሆ 24 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ማህበሩ ከተቋቋመ ጀምሮ በርካታ የስፖርት ፍቅርና ዝንባሌ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን በተለያየ ምድብ ከፍሎ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በብቃት እየተወጣ ይገኛል፡፡እድሜያቸው ከ35 ዓመት በላይ የሆኑ ግለሰቦችን በማካተት፤ እነዚህ ለሀገር መጠቀም የሚችሉ ዜጎችን ከአልባሌ ሱስና ከአላስፈላጊ ስብዕናዎች እንዲሁም ከተለያዩ ዓይነት በሽታዎችና ጭንቀት በመጠበቅ ረገድ ለህዝብና መንግስት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ይቀላቀሉን

ከጭንቀት የጠራ አዕምሮ

ጤናማ እና ከጭንቀት የጠራ አዕምሮ ያላቸውን የማህበረሰብ አባላትን በማፍራት ማህበራዊ ሃላፊነታችንን እየተወጣን እንገኛለን፡፡

ጤና

ራስዎን ከበሽታ እና ከጭንቀት ለመጠበቅ

ጓደኞችን የማፍራት

ጓደኞችን የማፍራት ሰፊ እድል እንዲኖርዎት ፤ ከሱስ እና ከአልባሌ ቦታዎች ይጠበቃሉ፤

ድርጅት አመሰራረት

የአዲስ አበባ የጤና ስፖርት ማህበር የተመሰረተው በ 1986 ዓ.ም ነው፡፡የአማኑኤል የጤና ቡድን በ1986 ዓ.ም ከስካኒያ የጤና ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ያቀረበው ግብዣ ተቀባይነት አግኝቶ ታሪካዊውን ጨዋታቸውን በአማኑኤል የጤና ቡድን ሜዳ ላይ ማድረጋቸው ዛሬ በአድናቆት ለምናየው የአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማህበር መቋቋም ምክንያት ሆኗል፡፡የሁለቱ ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ የስካኒያ ቡድን በሲሚንቶ ፋብሪካ ሜዳ ላይ ለማድረግ ግብዣውን አቅርቦ የመልሱ ጨዋታ ከተደረገ በኋላ በቅሎ ቤት ጠመንጃ ያዥ ባንክ ፊት ለፊት በሚገኘው ሀረግ ሆቴል የምሳ ግብዣ ባደረገበት አጋጣሚ ታሪካዊ ውይይት ተካሄደ፡፡በዚህ ግብዣ ወቅት ከሁለቱም ቡድኖች አንድ አንድ አባላት በሞት መለየታቸው ይነሳና ሁለቱ ቡድኖች ሁለት ሁለት ቡድኖች ይዘውና ሌላ ተጨማሪ ሁለት ቡድኖች ፈልገው በማካተት የመታሰቢያ ውድድር ለማድረግ የሚችሉበትን መንገድ የሚፈጥሩበት ሁኔታ እንዲኖር ሀሳብ ይቀርባል፡፡ይህ ሃሳብ በሁለቱም የቡድን አባላት ዘንድ ተቀባይነት በማግኘቱ ለተግባራዊነቱ እንቅስቃሴ የሚያደርግ አካል ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመታመኑ ከስካኒያ እና ከአማኑኤል የጤና ቡድኖች የተወከሉ አባላትን በማዋቀር የስራ ድርሻቸውን እንዲከፋፈሉ በማድረግ ስራው በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ተደርጎ የአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማህበር መሰረት ተጣለ፡፡

የተደራጀው ኮሚቴ ውድድር

ማህበሩ ከተቋቋመ በኋላ በ1987 ዓ.ም በተጠናከረ መልኩ የተደራጀው ኮሚቴ ውድድር ለማድረግ በማቀድ ተሳታፊ ቡድኖችን።
  • 1. አማኑኤል ጤና ቡድን (ሁለት ቡድኖችን ሀ እና ለ)
  • 2. ስካኒያ ጤና ቡድን ((ሁለት ቡድኖችን ሀ እና ለ)
  • 3. የመስቀል ወንድማማቾች
  • 4. መድኃኒዓለም ወንድማማቾች
  • 5. የተባበሩት ጓደኛሞች
  • 6. ጤንነት የጤና ስፖርት
  • 7. ሰሜን አዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማህበር
  • 8. ንፋስ ስልክ ጤና ስፖርት ማህበር
እነዚህን ቡድኖች በመያዝና አስቀድሞ ከነበሩበት ኮሚቴ አባላት በተጨማሪም አዳዲስ የተመዘገቡ ቡድኖች ማህበር ተጠሪ ጽ/ቤት በሚል አካል በማቋቋም ውድድሩን ማካሄድ ጀመረ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ የጤና ስፖርት ማህበር ተጠሪ ጽ/ቤት ምስረታን በማስመልከትም በወቅቱ የተገኙት የመስራች ማህበራት ተወካዮች የከተማዋ ስፖርት ማህበር የሚመራበትን የመቋቋሚያና መተዳደሪያ ደንብ ማውጣት አስፈላጊ መሆኑን በማመናቸውም የአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማህበራት ተጠሪ ጽ/ቤት መቋቋሚያና መተዳደሪያ ደንብ በ1987 ዓ.ም እንዲወጣ ተደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማህበር በየዓመቱ የሚያደርጋቸውን የክረምት ውድድሮችን በመምራት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከተለያዩ ማህበራት የተወጣጡ 43 ቡድኖችን በ3 ምድብ በመክፈል በማወዳደር ላይ ይገኛል፡፡

ከ50 ዓመት
ከ40 ዓመት በላይ
ከ35 ዓመት በላይ በማድረግ

ማህበሩ በስሩ 43 የጤና ቡድኖችን ያካተተ ሲሆን በፍቃደኛ እና ለጤና ስፖርት ትኩረት በሰጡ ታታሪ የረጅም ጊዜ አባላት እየተመራ ነው፡፡ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ያስመዘገባቸው ስኬቶች የአባላቱን ጥንካሬና የአመራሩን ሩቅ አሳቢነት ያሳያል፡፡

​‌“

45+ አባላት በላይ

  • የአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማህበር በየዓመቱ የሚያደርጋቸውን የክረምት ውድድሮችን በመምራት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከተለያዩ ማህበራት የተወጣጡ 43 ቡድኖችን በ3 ምድብ በመክፈል ከ50 ዓመት፤ከ40 ዓመት በላይ እና ከ35 ዓመት በላይ በማድረግ በማወዳደር ላይ ይገኛል፡፡

Request a call back.

Just submit your contact details and we’ll be in touch shortly. You can also email us if you prefer that type of communication.

ወቅታዊ ዜናዎች

ለጊዜው የዜና መረጃ የለንም